SportSports

በኮፓ ዴል ሬይ ሪያል ማድሪድ ሌጋኘስን አሸንፏል

በኮፓ ዴል ሬይ ሪያል ማድሪድ ሌጋኘስን አሸንፏል

በስፔን ኮፓ ዲል ሬይ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሲደረጉ ማድሪድ በሳንቲያጎ ቤርናባው ሌጋኘስን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ረትቷል፡፡

ለሎስ ብላኮስ የድል ግቦችን  አምበሉ ሰርጂዮ ራሞስ በፍፁም ቅጣት ምት፣ ሉካስ ቫዝኪውዝ እና ቬንሽዬስ ጁኒየር ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

በጨዋታው ቀዳሚዋን ግብ ያስቆጠረው ተከላካዩ ራሞስ በተጫዋችነት ዘመኑ 100ኛ ጎሉን አስቆጥሯል፡፡

በ15 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ ባለፈው ሳምንት ከማንችስተር ሲቲ ቤርናባውን የተቀላቀለው ስፔናዊው ወጣት ተጫዋች ብራሂም ዲያዝ፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 12 ደቂቃዎች ሲቀሩት ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ ግጥሚያውን አድርጓል፡፡

የመልሱ ጨዋታ በሚቀጥለው ሳምንት ዕረቡ ይካሄዳል፡፡

ወደ ካታላን ግዛት ያቀናው አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ጅሮና ጋር በአንድ አቻ ውጤት ተለያይቷል፤ አንቱዋን ግሪዝማን ለአትሌቲኮ አስቆጥሯል፡፡ ሄታፌ ሪያል ቫያዶሊድን 1 ለ 0 ሲረታ፣ ቪያሪያል ከ አስፓኞል 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button