
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በአፍሪካ ሀገራት ላይ ጥለውት የነበረውን የጉዞ ክልከላ ማንሳታቸው ተሰማ፡፡
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባይደን በይፋ እንደተናገሩት የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች በኦሚክሮን ቫይረስ ቢያዙ እንኳ ለከፋጉዳት እንደማይዳረጉ የህክምና ባለ ሙያዎች አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በደቡባዊ አፍሪካ ከሚገኙ ስምንት ሀገራት የሚመጡ ተጓዦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡጥለነው የነበረው እገዳ ከእግዲህ አይሰራም ተጓዦቹ መከተባቸው በቂ ነው ብለዋል፡፡ዋሽንግተን የጉዞ ክልከላ ጥላባቸው የነበሩት ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባቡዌ፣ ናሚቢያ፣ሌሴቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሞዛምቢክና […]