AfricaUncategorized

ሩዋንዳ በሃገሯ የሚካሄደውን የነዳጅ ዘይት ፍለጋ ስራ አስቆመች

አርትስ 13/02/2011
ሃገሪቱ ፍለጋው በሚካሄድበት ሊቩ ሃይቅ አካባቢ አለም አቀፍ ነዳጅ ኩባንያዎች እንዲሰማሩ አድርጋ ነበር።

የሩዋንዳ ማዕድን ቦርድ ስራ አስፈጻሚ ፍራንሲስ ጋትሬ እንደሚናገሩት መንግስታቸው ይህንን ያደረገው ሃገሪቱን ሊገጥማት የሚችለውን የፋይናንስ እጥረት ለመቀነስ ሲል ነው።

ሩዋንዳ ከውሳኔዋ በኋላ በሃይቁ አካባቢ የሚካሄደውን የነዳጅ ፍለጋ ቅድመ ጥናት በራሷ ልታካሂድ አስባለች።

ቅድመጥናቱ የሚፈልገው ወጪ አነስተኛ ነው። ስለሆነም ያንን በራሳችን ባለሙያና ላቦራቶሪ ማካሄድ እንችላለን።በአካባቢው ነዳጅ መኖሩን ካረጋገጥን በኋላ ኩባንያዎቹን መልሰን እንጋብዛቸዋልን ነው የሚሉት ስራ አስፈጻሚው።

እገዳው ጊዜያዊ መሆኑን የተናገሩት ስራ አስፈጻሚው በተለይ መንግስት ነዳጅ ቢገኝ ድርሻው ሰፊ እንዲሆን ፍለጋውን ከሚያካሂዱት አለምአቀፍ ተቋማት ጋ በትብብር መስራት በሚያስችለው ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።

ነዳጅ ፍለጋ በግል ኩባንያዎች መካሄድ እንዳለበት ብናምንም መንግስትም ከዚህ ስራ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ መሆኑን እናምናለን ነው የሚሉት ፍራንሲስ።

ቅድመጥናቱን እኛ ማድረግ የፈለግነው ለግል ኩባንያዎች በቂ መረጃ ለማሰባሰብ መንግስትም ትርጉም ባለው መልኩ አብሮ ለመስራት የሚችልበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው ብለዋል።

በሩዋንዳ ውሳኔ እንደቱሎው ያሉ አለምአቀፍ ነዳጅ አምራች ኩባንያዎች ከአሁኑ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

የሩዋንዳ የነዳጅ ህግ የነዳጅ ማውጫ ስፍራዎች ባለቤትነት በመንግስት ካልሆነ በቀር በግል እንዳይያዙ ይከለክላል።

በዚያች ሃገር ለየትኛውም የውጭ ኩባንያ የነዳጅ ፍለጋ ፍቃድ የሚሰጠው ለሶስት ዓመታት ብቻ ሲሆን ማምረት የሚችለው ደግሞ ለ25 ዓመታት ብቻ ነው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button