loading
ሐሰት: ይህ ምስል የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ በድሮን መመታቱን አያሳይም።

የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ምንም አይነት በከባድ የጦር መሳርያ የደረሰ ጉዳት የለም። በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “#ሰበር #ዜና የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው ቡድን የተከዜ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተገለፀ። የህውሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸዉ ረዳ በቲዊተር ገፃቸዉ እንደገለፁት ከሆነ ዛሬ ጣዋት አከባቢ ጥቃቱ በግድቡ […]

ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ። የልዩ ዘመቻዎች ኃይል፣ የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይል እና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሌተናል ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት የመጀመሪያው […]

የሽብር ቡድኑ በጭና እና ቆቦ ንፁሃንን በጅምላ ጨፍጭፏል – ሂዩማን ራይትስ ዎች ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 ሂዩማን ራይት ዎች የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበረው የአማራ ክልል ጭና እና ቆቦ ከተሞች ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን ገለፀ፡፡ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ከፈረንጆቹ ነሐሴ 31 እስከ መስከረም 9 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፡፡ ከዚህም ውስጥ የጭና ቀበሌ […]

የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ። የዓለም ዐቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታኅሣሥ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱ እየተጠናቀቀ ነው ያለው ቢሮው፤ […]

የኢትዮጵያን ስም የሚያጠለሸው አዋጅ ውድቅ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 ኢትዮጵያን በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ መሰረዙ ይፋ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡ በመረጃውም በኢትዮጵያ “የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሂዷል” በሚል ሀሰተኛ ውንጀላ ኢትዮጵያን ለመጠየቅ የሚረዳና በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው ሕግ ማለትም […]

አራት የፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር አስረከቡ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 አራት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር ማስረከባችው ተገለጸ፡፡ በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል ከሕዝብ እና ከመንግሥት የተሰጠን አደራ ነው ያሉት አራቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺሕ 900 የአሜሪካ ዶላር ማስረከባቸውን ፖሊስ አስታውቋል።ምክትል ኢንስፔክተር ዘነበ እሸቱ፣ ምክትል ኢንስፔክተር ዳግም ግርማ እና ዋና ሳጅን […]

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለዳያስፖራዎች እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ለገናና ጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራዎች እስከ ሰላሳ በመቶ የሚደርስ ልዩ ቅናሽ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ገለጸ። የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሀ በቀለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትእንደገለጹት፤ በመዲናዋ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለገናና ለጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ […]

ጥይት ያለአግባብ አታባክኑ-ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 ሁሉም ለቀጣይ ትግል በሚዘጋጅበት ወቅት ጥይት ያለ አግባብ ማባከን አይገባም ሲሉ የአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አሳሰቡ፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫ ከአሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ቡድን ጋር በተካሄደው ፍልሚያበጀግንነት ተጋድሎ ያደረጉ የጸጥታ አካላት ለከፈሉት መስዋእትነት ትልቅ ክብር አለን ብለዋል። በግንባር ለተፋለሙ ጀግኖች አቀባበል ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ለአቀባበል በሚል የጥይት ተኩስማድረግ ማኅበረሰቡን […]