loading
አሜሪካ ለገበሬዎቿ ካሳ ልትከፍል ነው

ዋሽንግተን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት ኪሳራ ለደረሰባቸው ገበሬዎች 12 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መወሰኗ ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በግብርና የሚተዳደሩ አሜሪካውያን ምርታቸውን ወደ ውጭ ሀገር ልከው እንዳይሸጡ አዲሱ የንግድ እሰጣ ገባ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡ በተለይ የአሜሪካን የግብርና ምርቶች ወደ ሀገሯ ታስገባ የነበረቸው ቻይና፤ ትራ ምፕን ለመበቀል የጣለችው ታሪፍ በገበሬዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮባቸዋል፡፡ የታሪፍ […]

በግብጽ እስር ቤቶች በጤና ችግር ሳቢያ የሚሞቱ እስረኞች ቁጥር እየጨመረ ነዉ

ምክንያቱ ደግሞ ያልተገባ አያያዝ፣ የህክምናና የመድሀኒት እጥረት መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናግረዋል፡፡ የእስረኞቹ ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን የጤና ሁኔታ ተከታትለው እንዳይመዘግቡና መረጃ እንዳያገኙ እየተደረጉ ነው ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡ በግብጽ የአንድ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ መሪ የነበሩት አብደል ሞኔም አቡል ፎቱህን የጤና ሁኔታ በማሳያነት ያነሳሉ የመብት ተሟጋቾቹ፡፡ ግለሰቡ በፌስ ቡክ ገጻቸው የእስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች ሆስፒታል ሄጄ እንዳልታከም […]

በግሪክ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል

በቦታው የተሰማሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች እንዳሉት በዋና ከተማዋ አቴንስ አቅራቢያ በተከሰተው አደጋ እስካሁን 49 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል ህጻናት የሚበዙ እንደሆነ ታምኗል፡፡ ሲ ኤን ኤን በዘገባው እንዳሰፈረው በግሪክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2007 ወዲህ እንደዚህ ዓይነት የከፋ የእሳት አደጋ አጋጥሞ አያውቅም፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ 156 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ ከነዚህ መካከል ደግሞ አስራ አንዱ […]

ሰሜን ኮሪያ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿዋን ማፍረስ መጀመሯ ተሰማ

የሳተላይት ምስል እንደሚያሳየው ፒዮንግያንግ ቁልፍ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿን እያፈረሰች መሆኗ ተረጋጋጧል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በተችዎቻቸው ዘንድ መቆሚያ መቀመጫ ላጡት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ትልቅ እፎይታ ነው፡፡ በሁኔታው የተደሰቱት ትራምፕም እኔ ያላልኩትን የሚያራግቡና የሀሰተኛ ወሬ የሚያናፍሱ በሰሜን ኮሪያ ድርጊት ተበሳጭቷል ለሚሉ ሁሉ ይሄው እኔ ደስተኛ ነኝ የሚል ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ይሁንና የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ የምታፈርሰው […]

የሞሮኮ አየር መንገድ ለዛሬ ተይዘው የነበሩ በረራዎችን ለመሰረዝ ተገዷል

ምክንያቱ ደግሞ አብራሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ነው ብሏል የሞሮኮ ሮያል አየር መንገድ በድረ ገጹ ባሰራጨው ጽሁፍ፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አብራሪዎቹ ስራ ለማቆም ያስገደዳቸው ላቀረቡት የደሞዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ ከአሰሪ ድርጅታቸው አጥጋቢ መልስ አለማግኘታቸው ነው፡፡ በድርጅቱና በሰራተኞቹ መካከል ለወራት የዘለቀ ድርድር ቢደረግም መግባባት አልተቻለም ብለዋል የአብራሪዎች ማህበር አመራሮች፡፡ አየር መንገዱም ሰራተኞቹ ወደ ስራ ገበታቸው […]

አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በ5ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔው አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን የክልሉ ርዕሰ መስተደሳድር አድርጎ ሾሟል። አቶ ሚሊዮን ቃለ መሃላ በመፈፀም ቀደም ሲል ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ ከነበሩት አቶ ደሴ ዳልኬ ኃላፊነቱን ተረክበዋል። አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በቅርቡ ክልሉን የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው […]

በስብሰባ መሀል ዘና በሉና ተሸለሙ

ዛሬ ጠ/ሚኒስትሩ ከመምህራን ጋር የነበራቸው ቆይታ የቻይና ጉዞ ሽልማቶችም እንደነበሩት ሰምተናል፡፡ ዶ/ር አብይ ከጋበዟቸው እና ወደ መድረክ ከወጡት ስምንት መምህራን “ፑሽ አፕ” ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር የሰሩ እና ያልደከሙ ሦስት መምህራን ቻይና ለ 15 ቀን ስልጠና እንደሚሄዱ ተነግሯቸዋል፡፡ በወንዶቹ ሳያበቃ ለተመሳሳይ ውድድር ሲጋበዙ ተሸቀዳድመው የወጡ ከ36 በላይ ሴቶችም ለሁሉም የቻይና የጉብኝት ዕድል እንደተሰጣቸው ሰምተናል፡፡

ማይክ ፖምፒዮ የኢራንን መሪዎች ከማፊያ ጋር አመሳስለዋቸዋል

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ የኢራን መሪዎች ከመንግስትነት ይልቅ የማፊያ ባህርይ ጎልቶ ይንጸባረቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ፖምፒዮ ለዚህ አባባላቸው በሀገሪቱ ያለውን ሰፊ ሀብትና የመሪዎቹን በሙስና መዘፈቅ በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ፖምፒዮ ካሊፎርኒያ ውስጥ ባደረጉት ቅስቀሳ የሚመስል ንግግር ኢራናውያን የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ ራሳቸው መወሰን አለባቸው፤ እኛ አሜሪካውያንም ከጎናቸው እንቆማለን ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በየፊናቸው አንዱ […]

በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኛች ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀመሩ፡፡

የፕሬዝዳን ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ባወጣው ህግ ሰነድ አልባ ስደተኞች በማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ ህጻናቱ ለብቻቸው እንዲኖሩ ተገደው ነበር፡፡ አሁን ግን የአሜሪካ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት እድሜያቸው ከ5-17 ያሉ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀምረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው እስካሁን 1ሺህ 800 ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር የመቀላቀል ዕድል አግኝተዋል፡፡ 2ሺህ 500 ህጻናት ወላጆቻቸው ህገ ወጥ ናችሁ ተብለው በስደተኞች ማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ […]