loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡናን በአለም ገበያ ላስተዋዉቅ ነዉ አለ

” አለም አቀፍ የቡና ቀን በምድረ ቀደምት” በሚል ቡናን ለማስተዋወቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ በአየር መንገዱ የኮርፖሬ ት ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር አቶ አደፍርስ ታዬ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በፕሮግራሙ የአየር መንገዱ ሰራተኞች፣የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት በመገኘት የኢትጵያን ቡና በአለም ገበያ ማስተዋወቅን በተመለከተ ይመክራሉ ፡፡

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተም በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀዋል፣ እንግሊዝ ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቴሌኮም ዘርፍ ለስምንት ዓመታት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ከመምራት አንስቶ፣ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ድረስ ማገልገላቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም ሕዝብ ግንኙነት ክፍል […]

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ሆቴሎች ባህልን የሚያንፀባርቅ ገፅታ ሊኖራቸዉ ይገባል ተባለ

ይህ የተባለዉ የካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል አዳራሹን ሲያስመርቅ ነው፡፡ በካፒታል ሆቴል የባህል አደራሽ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ የተገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋ ዳግማዊትም ከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ባህል አዳራሾች ያስፈልጓታል ፤በባህል ላይ የሚሰሩ ባለሀብቶችንም እናበረታታለን ብለዋል፡፡ የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስአለም ገብሬ በሆቴላቸዉ ዉስጥ ልዩ […]

የኢንጀነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ – ሥርዓትን እሁድ ሀምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ይፈጸማል

የኢንጀነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ – ሥርዓትን እሁድ ሀምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ይፈጸማል ፡፡ ብሔራዊ የቀብር አስፈሚ ዐብይ ኮሚቴ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ የቀብር ሥነ-ስርአቱ ዕሁድ ሐምሌ 22 ቀን 2010. ከቀኑ 7፡00 ሰአት በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሥራ ባልደረቦች እና መላው ህዝብ በተገኙበት […]

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡ ይህንን ያላችሁ የኢፌድሪ የንግድ ሚኒስቴር ነዉ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በላከልን መግለጫ ስንዴ ፣ስኳርና ፓልም ዘይት በመንግስት ድጎማ ወደሀገር ዉስጥ እየገባ ቢሆንም ፤ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባደረገዉ አሰሳና በህዝብ ጥቆማ መሰረታዊ ሸቀጦቹ እየተደበቁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩም መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን የምትፈጽሙ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆነ የሸማቹን […]

የባንኮች አጠቃላይ ሀብት አንድ ትሪሊዮን ብር ደረሰ::

የግል ባንኮች ብድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰጠው መብለጡም ተሰምቷል፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበዉ የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪና የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ እንደገለጹት፣ አሥራ ስምንቱ የአገሪቱ የግልና የመንግሥት ባንኮች በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ያስመዘገቡት የሀብት መጠን አንድ ትሪሊዮን ብር ሊደርስ የቻለው በ2002 ዓ.ም. ከነበረበት 167 ቢሊዮን ብር ተነስቶ […]