EthiopiaLegalRegionsSocial

ዛሬ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቁጣቸውን በአደባባይ እየገለፁ ይገኛሉ

ዛሬ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቁጣቸውን በአደባባይ እየገለፁ ይገኛሉ

አርትስ 28/02/2011
ህዝቡን አደባባይ ያወጣው ሳላይሽ በተባለው አካባቢ በአንዲት ዕድሜዋ ሰባት ዓመት እንደሆነ በተነገረን ታዳጊ ላይ የተፈፀመ አሰቃቂ ድርጊት ነው፡፡ አንድ ጎልማሳ
ታዳጊዋን አስገድዶ ከደፈረ በኋላ እንደገደላት ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎችም በግለሰቡ ድርጊት ተቆጥተው በፒያሳ እና አውቶቡስ ተራ ጎዳናዎች ወጥተዋል፡፡ ወደፖሊስ ጣቢያም በማምራት ፈጣን ርምጃ እንፈልጋለን ሲሉ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት መንገዶች ተዘጋግተዋል፡፡
ፎቶ ፦አመብድ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button