loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛሉ፡፡

የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለድሉ ጅማ አባጅፋር እ እንደ ኦኪኪ አፎላቢ እና መሰሎቹ ወደ ሌላ ክለብ ማምራታቸውን ተከትሎም የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት እስካሁን በአጠቃላይ 11 ያህል ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ በትላንትናው ዕለትም ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተሰናበቱት አሉላ ግርማ እና ዘሪሁን ታደለ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቡናው አስቻለው ግርማ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሁነዋል። ወደ ዋናው […]

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ጥሪ አቀረቡለት

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸውን ያስታወቁት። በመግለጫቸውም በሪዮ ኦሎምፒክ እና በልዩ ልዩ የዓለም አትሌቲክስ መድረኮች በመሳተፍ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስተዋጽኦ ያበረከተው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ፍላጎታቸው መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጁት […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጌታነህ ከበደን አስፈረመ፡፡

የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ እና የደደቢት እንዲሁም በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ የደቡብ አፍሪካዎቹን ቢድቬስት ዊትስ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ጌታነህ ከበደ (ሰበሮ) በዛሬው ዕለት ለ2 ዓመት ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ጌታነህ ደደቢት ቡድኑን በአዲስ መልክ ለማደረጀት፤ በአነስተኛ ክፍያ ወጣቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ ፈረሰኞቹን ተዋህዷል፡፡ የ26 አመቱ ተጫዋች […]

የዘንድሮ የኢ.ቢ.ሲ የስፖርት ሽልማት በመጪው መስከረም በሸራተን አዲስ እንደሚደረግ ይፋ ሆነ፡፡

በ 2009. ዓ.ም የተጀመረው የኢ.ቢ.ሲ የአመቱ ምርጥ የስፖርት ሽልማት በዘንድሮ አመትም ለሁለተኛ ጊዜ በአምስት ዘርፎች እንደሚያካሄድ ኮርፖሬሽኑ አስታዉቋል፡፡ የኢ.ቢ.ሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ጋር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በእግር ኳስ ዘርፍ እና በአትሌትክስ ዘርፍ በሁለቱም ፆታዎች ፤ከአምናው በተለየ ደግሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍም በዘንድሮዉ ሽልማት ተካቷል፡፡ እነዚህን እጩዎች […]

በ2019 የታዳጊዎች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ፡፡

በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታው የኡጋንዳ ቡድንን 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በሁለተኛ ጨዋታው ጅቡቲን 4 ለ 0 በመርታት ወደ ተከታዩ ደረጃ ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡ የቀይ ቀበሮዎቹን የድል ጎሎች በየነ ባንጃ፤ በረከት ካሌብ፤ ቢንያም አይተን፤ መንተስኖት እንድርያስ አስቆጥረዋል፡፡ እዚሁ ምድብ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በቀጣይ መጭው እሁድ ነሃሴ 13 በቻማዚ […]

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነዉ፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበዉ አትሌት ፈይሳ በቅርቡ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ሀገር ቤትለመመለስ ወስኗል፡፡ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በጋራ ባወጡት መግለጫ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ወደ ሀገሩ እንዲመለስ መጋበዛቸዉ ይታወሳል፡፡በወቅቱም ለአትሌቱ የጀግና አቀባባል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ::

የምድብ ሀ አሸናፊ ባህርዳር ከነማ(የጣናው ሞገድ) ከምድብ ለ አሸናፊ ደቡብ ፖሊስ የሚያደርጉት የፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ይሄ ጨዋታ ቀድሞ በወጣው መርሃ ግብር ድሬዳዋ ላይ ይደረጋል የተባለ ቢሆንም የድሬዳዋ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት መታረሱ የቀንና የቦታ ለውጥ ለመደረጉ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት የባህርዳር ከነማና የደቡብ ፖሊስ የዋንጫ ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ […]