EthiopiaPoliticsRegionsSocial

አቶ ጀዋር መሀመድ በሻሸመኔ የተፈጸመዉን ድርጊት አወገዘ፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ለሰዉ ህይወት መጥፋትና የአካል መጉደል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡም በፌስቡክ ገጹ ጠይቋል፡፡
አቶ ጀዋር የሻሸመኔ ህዝብ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ተቀብሎናል፤ነገርግን በከተማዋ ሊቀበለን የወጣዉ ህዝብ ቁጥር ከተጠበቀዉ በላይ በመሆኑና በህዝቡም መካከል ሀሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል፤ አካል ጉዳትም ደርስዋል ፤ በዚህም በጣም ማዘኑን ተናግሯል፡፡
ተጨባጭ ባልሆነ መረጃ ንጹህ የሆነ ሰዉን መጉዳት ትልቅ ታሪክ ያላትን ከተማ ስም የሚያጠለሽ ነዉ ሲል አቶ ጀዋር የገለጸ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም በሌሎች ከተሞችም ምንም አይነት ጉብኝት እንደማያደርግ አስታዉቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button