loading
የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዋር ጋርጋሽ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ወቅት በቴልአቪቭ ኤምባሲያችንን እንከፍታለን ማለታቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ከእስራኤል ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውሰው፤ በዓለም አቀፍ መርህ ሁለት ሀገራት ሊኖራቸው በሚገባው ግንኙነት መሰረት አቡዳቢ በቴላቪቭ ኤምባሲዋን ትከፍታለች ብለዋል፡፡ሚኒስትሩ […]

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::በወቅታዊ የማሊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደረገወ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አባል ሀገራት (ኢኮዋስ) የማሊወታደሮች ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን በቁጥጥር ስር አውሎ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዟል፡፡ ኢኮዋስ በትላንትናው ዕለት ባደረገው የቪድዮ ስብሰባ ፕሬዝዳንቱ ቡበከር ኬታና በእስር የሚገኙ ባለስልጣናት […]

ማይክ ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 18፣ 2012 ማይክ ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ፡፡በእየሩሳሌም ከእስራኤሉ አቻቸው ጋር የተገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት ፣ በባህሬንና በሱዳን ጉብኝት እንደሚያደርጉም ይጠበቀል፡፡ፖምፒዮ በመካከለኛው ምስራቅ ለአምስት ቀናት የሚያደርጉትን ጉብኝት ከእስራኤል የጀመሩ ሲሆን ጉብኝቱም በእስራኤልና አረብ ሀገራት መከካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡ እንደ አልጄዚራ ዘገባ የውጭ ጉዳይ […]

ሱዳን ከዓለም ዓቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ ጋር በጦር ወንጀሎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማማች፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 18፣ 2012 ሱዳን ከዓለም ዓቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ ጋር በጦር ወንጀሎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማማች፡፡ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሃምዶክ ዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሱዳን ዳርፉር ተከስቶ በነበረው ግጭት የጦር ወንጀሎችንና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የፈጸሙትን አካላት ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር […]

ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ የአለም ጤና ድርጅት አፈሪካ ከፖሊዮ ነጻ መሆንዋን መግለጹን ተከተሎ ነዉ ፖሊዮን ለማጠፋት ለሰሩት የጤና ባለሞያዎች ለማህበረሰብ መሪዎች እና አባላት ወላጆችና አሳዳጊዎች እነዲሆም ለአጋር አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡ አፍሪካ የዋይልድ ፖሊዮ ቫይረስ መጥፋት ማረጋገጫ የሆነዉን የምስክር ወረቅ መቀበሏንም ዶክተር ሊያ […]

የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡ ኤጀንሲዉ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤ለመንገድ ፈንድ በአዋጅ ከተለዩ የገቢ ምንጮች አንዱ ክብደትን መሰረት ካደረገ አመታዊ የተሽከርካሪዎች ፈቃድ ማደሻ ክፊያ የሚገኝ ገቢ ነው እሱም እየተጭበረበረ ነዉ ብሏል፡፡ ይሄንን ገቢ ከኢትዮጵያ ፖስታ ቤት ጋር የመንግድ ፈነደ ጽ/ቤት […]

ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመግለጫቸው እንዳሉት በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የምት ከለቦችና መጠጥ ቤቶች ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ፡፡ በሰርግ፣ በቀብር ስነ ስርዓቶችና በሌሎችም ሁነቶች ላይ የሚገኙ ሰዎች ግን ቁጥራቸው ካልበዛና እርቀታቸውን እስከጠበቁ ድረስ አይከለከሉም ነው የተባለው፡፡ ኬንያታ ምንም እንኳ በሀገራችን የቫይረሱ […]

የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ:: የነጭ የበላይነትን አብዝቶ የሚያቀነቅነው ብሬንተን ታራንት የተባለው የ29 ዓመት ወጣት የፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያለ ምንም መከራከሪያ አምኖ ለፍርድ ቤቱ ቃሉን በመስጠቱ ነው ጥፋተኛ የተባለው፡፡ ይህ አውስትራሊያዊ ወጣት ክሪስት ቸርች በተባለ ስፍራ ለፀሎት በተሰባበሱ ሙስሊሞች ላይ በከፈተው ድንገተኛ ተኩስ 51 ሰዎችን መግደሉን […]

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ፈንድ ያላግባብ አባክነዋል በተባሉ ባለ ስልጠጣናት ላይ ምርመራ ልትጀምር ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 22፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ፈንድ ያላግባብ አባክነዋል በተባሉ ባለ ስልጠጣናት ላይ ምርመራ ልትጀምር ነው:: የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ይፋ እንዳደረጉት ኮሮናቫይረስን መከላከል ለሚያስፈልጉ ወጭዎች የተመደበው ገንዘብ ለሙስና ተጋልጧል፡፡በመሆኑም ልዩ የምርምራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እነዚህን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ባለ ስለጣናትን መርምሮ ለህግ እንዲያቀርብ አዘዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ለጭንቅ ጊዜ የተመደበን […]