loading
ግብጻዊው ጸሀፊ ግብጽ ወደ ንጉሳዊ የአገዛዝ ዘመን እንድትመለስ ጥያቄ አቀረበ፡፡

ዳንድራዊ አል ሀዋሪ የተባለው ግብጻዊ ደራሲ ሀገሪቱ ወደ ቀድሞው ስርዓት ስትመለስ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ደግሞ ንጉስ ሆነው መሰየም አለባቸው የሚል ሃሳብም አቅርቧል፡፡ የደራሲውን ሀሳብ ብዙዎች አውግዘውታል፣ በርካቶችንም ለብስጭት ዳርጓል ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡ ከአስተያየት ሰጭዎቹ መካክል እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ግብዝነት የተሞላበትና ሀገሪቱን የማይጠቅም ነው በማለትም አጣጥለውታል፡፡

ተወዳጁ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ከ1948-2010 ከመድረኩ ንጉሳችን ፣ንጉሥ ቴዎድሮስን፣ንጉሥ ኤዲፐስን ፣ንጉሥ ሐምሌትን፣ ንጉሥ አርማህን በህይወት አጣናቸዉ፡ መቃብር ቆፋሪውና የሬሳ ሳጥን ሻጩ፣ እሳት ሲነድ፣ ቤቴ፣ የሠርጉ ዋዜማ፣ ደማችን፣ የሊስትሮ ኦፔራ፣ አቡጊዳ ቀይሶ፣ ባለካባ ባለዳባ፣ መልዕክት ወዛደር፣ ታርቲዩፍ ከተወነባቸው ይገኙበታል፡፡ ኪነ ጠቢቡ ፍቃዱ ተክለማርያም በቴሌቪዥን ከተወናቸው ተውኔቶች መካከልም ያልተከፈለ ዕዳ፣ የአበቅየለሽ ኑዛዜ፣ ባለጉዳይና በሕዝብ ዘንድ አድናቆትን ያተረፉለት ናቸው፡፡ […]

ሪያድ የሀጂ ጉዞን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይቻልም አለች፡፡

ሪያድ የሀጂ ጉዞን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይቻልም አለች፡፡ የሳውዲ አረቢያ የኢንፎርሜሽን ሚንስትር አዋድ ቢን ሳልህ አልዋድ እንዳሉት ወደ ቦታው የሚጓዙ ምእመናን ከጉዞው ሀይማኖታዊ በረከት እንጂ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ እንዳይደክሙ አሳስበዋል፡፡ ሚንስትሩ ይህን ያሉት ጅዳ ውስጥ ከአረብ ከአፍሪካና ከእስያ ሀገራ የተወከሉ ልኡካን ጋር ተገናኝተው በጉዞው ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡ አልዋድ እንዳሉት ሀገራቸው ከየትኛውም የዓለም ክፍል ወደ […]

ሰሜንኮሪያ አዲስ የሚሳኤል ግንባታ ጀምራለች ተባለ፡፡

ሰሜንኮሪያ አዲስ የሚሳኤል ግንባታ ጀምራለች ተባለ፡፡ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣንት ነገሩኝ ብሎ ዋሽንግተን ፖስት ነው ዜናውን ያሰራጨው፡፡ ባለስልጣናቱ የሰሜን ኮሪንያን የባለስቲክ ሚሳኤል ግንባታ እንቅስቀሴ በድብቅ ሳተላይት ደርሰንበታል ብለዋል ሲል የዘገበው ደግሞ ሮይተርስ ነው፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ታሪካዊ የተባለውን ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእንግዲህ መላው ዓለም የሰላም እንቅልፍ ይተኛ ምክንቱም የኒውክሌር ስጋት አክትሟል ብለው […]

አገሪቱ በአምቡላንስ ቁጥር የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት አሟልታለች ተባለ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 746 አምቡላንሶችን ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለት ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ለስምንት ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች አከፋፍያለሁ ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ ሌሎች 407 አምቡላንሶች ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት በመጓጓዝ ላይ ናቸው ሲል አስታውቋል፡፡ ይህም ማለት ቀደም ሲል ከተሰራጩት 1200 አምቡላንሶች ጋር ሲደመር ከሁለት ሺህ በላይ ይሆናል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልፆ የ1859 ተጨማሪ አምቡላንሶች በግዥ በሂደት […]

ዛኑፒኤፍ አብላጫውን የፓርላማ መቀመጫ አሸንፏል ተብሏል፡

በዚምባቡዌ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ማሸነፉ ይፋ ሆኗል፡፡ ሮይተርስና አልጀዚራ ከሀራሬ የሀገሪቱን የምርጫ ኮሚሽን ጠቅሰው እንደዘገቡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሚመሩት ዛኑ ፒፍ ፓርቲ 109 መቀመጫዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ የተሰኘው ተቃዋሚ ፓርቲ ደግሞ 41 መቀመጫዎችን አሸንፏል ነው የተባለው፡፡ ቀሪዎቹን 58 መቀመጫዎች ማን እንዳሸነፈ ገና ያልተገለጸ ሲሆን […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ የነበረን ቆይታ አድካሚ ቢሆንም ስኬታማ ነበር ሲሉ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ የነበረን ቆይታ አድካሚ ቢሆንም ስኬታማ ነበር ሲሉ ተናገሩ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ለመገኛኛ ብዙሀን እንደተናገሩት እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሁሉ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆንም በኃላፊነት እንሰራለን ብለዋል፡፡ ለነበራቸው ቆይታ ድጋፍ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡