loading
በሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ የምርመራ የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ ተሰጠ::

የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በሰኔ 16ቱ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የስራ ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በተጠረጠሩት ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆ የመጨረሻ የሶስት ቀን ጊዜ ብቻ ተፈቅዷል።

በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰትና ኩብለላ ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ፥ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊት ለውጡን በመደገፍ እየሰራ ነው። የምህረት አዋጁ […]

በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው::

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች […]

ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ አስታወቀ

ሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የአመራርነት ክፍተት አሳይተዋል ተብለው ምርምራ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በዋስ ቢለቀቁ አቃቤ ህግ እንደማይቃወም ገለጸ፡፡ አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አስታውቋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም በጉዳዩ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጿል፡፡ […]

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡

ባለፉት ዓመታት በተጠርጣሪዎችና በታራሚዎች አያያዝ ላይ ያሉ ችግሮች መሻሻል አልታየባቸውም ተባለ::

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ከሚሽን በቢሸፍቱ ከተማ ለፌደራልና ክልል የጸጥታ ተቋማት ሀላፊዎች ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ ነዉ ። ስልጠናው በአትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን ማክበርና ማስከበር ላይ ያተኮረ ሲሆን ለአምስት ቀናት የሚሰጥ ነው ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር ስልጠናዉን ሲከፍቱ ሰልጣኞቹ ሰብዓዊ መብት መከበርና ማስከበር ላይ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል ። ስልጠናው […]

የተሽከርካሪ አደጋ አስከፊ እየሆነ በቁጥርም እያሻቀበ ነው፡፡

በአገራችን 2010 ዓ.ም 40ሺህ 998 የተሸከርካሪ አደጋ ደርሷል፡፡ 5ሺህ 118 ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡ 7ሺህ 754 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 7ሺህ 775 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ 920 ሚሊዮን 771 ሺህ ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወድሟል፡፡ ባለፈው ዓመት 2009ዓ.ም የደረሰው አደጋ 38ሺህ 737 ነበር፡፡ አቶ ይግዛው ዳኘው የትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት […]