loading
ቻይና የጸረ ሚሳኤል ሙከራና የቀጠናው ውጥረት ማገርሸት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 የ ቻይና የተሳካ የመካከለኛ ርቀት የጸረ ባለስቲክ ሚሳኤል ሲስተም ሙከራ ማድረጓን ይፋ አደረገች፡፡ የቻይና መካለከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሙከራው ቤጂንግ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣባት የሚችለውን የሚሳኤል ጥቃት መከላከል ላይ ያተኮረ ነው ብሏል፡፡ ሙከራው የታቀደለትን ግብ ያሳካ ነበር ያለው ሚኒስቴሩ ዓላማውም መከላከልን እንጂ በየትኛውም ሀገር ላይ ስጋት ለመፍጠር እንዳልሆነ ይታወቅልን ነው ያለው፡፡ […]

የህንድ ፍርድ ቤት 38 ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 የህንድ ፍርድ ቤት 38 ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡ ግለሰቦቹ ይሙት በቃ የተወሰነባቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2008 ከ50 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ነው፡፡ በጉጂራት ግዛት በምትገኘው የአህመዳባድ ከተማ በደረሰው ጥቃት 56 ሰዎች ሲገደሉ 200 የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ […]

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014 በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሮጲ ከተማ የተገነባው የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተመረቀ::የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ግንባታቸዉ ከተጀመሩት ትምህርት ቤቶች መካከል የመጀመሪያ የሆነዉን በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን ሮጲ ከተማ የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ነው ያስመረቀው፡፡ የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በሰባት ወር ጊዜ […]

ለመከላከያ ሰራዊት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ተደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰባሰበውን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አስረከበ ከድጋፉ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን የሚሆነው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን እና 180 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ደግሞ በዓይነት ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩን ድጋፍ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ተረክበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር […]

ጦርነቱ ህዝባዊ ይደረግ ተባለ::

የአማራ ክልል ህዝብ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው ርዕሰ መስተዳደር ጥሪ አቀረቡ:: የህወሓት የሽብር ቡድን ጦርነቱን ህዝባዊ ስላደረገው የአማራ ክልል ህዝብም በተመሳሳይ መንገድ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የህወሓት የሽብር ቡድን በዋናነት በሶስት ግንባሮች ማለትም በሰሜን እና በደቡብ ጎንደር እንዲሁም በሰሜን ወሎ ወረራ መፈፀሙን ገልፀዋል፡፡ […]

በህገወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም  ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀውን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች እና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል። በአካባቢው የሚኖሩ አምስት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት ፈልገው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት ምስራቅ ዲስትሪክት አመልክተው ተራ በመጠበቅ […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው በጉባኤው ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ተገኝተዋል። ወይዘሮ ሙፈሪያት የኢትዮጵያ የሐይማኖት ጉባኤ ምዕመናን ችግር ሲገጥማቸው ከችግር የሚወጡበትን መንፈሳዊ ጥንካሬን ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንና ባለፉት ሦስት ዓመታት የገጠሙንን ችግሮች […]

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች-ጠ/ሚ ዐቢይ ጠ/ሚ ዐቢይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች ብለዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሁለተኛ […]

የተለያዩ ክልሎች ልዩ ሀይሎች ወደ ግዳጅ ቀጠናዉ እያመሩ ነዉ::

የተለያዩ ክልሎች ልዩ ሀይሎች ወደ ግዳጅ ቀጠናዉ እያመሩ ነዉ::የኦሮሚያ እና የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይሎች ወደ ግዳጅ ቀጠና አመሩ በተያያዘም የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል ግዳጅ ቀጠናው ላይ ደርሷል፡፡በተመሳሳይ የሀገርን ሰላም ለማስከበር የተንቀሳቀሰው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይልም ቀደም ብሎ ግዳጅ ቀጠና መድረሱ ይታወሳል፡፡ አሸባሪዉን ቡድን ለመዋጋት የአማራ ክልል ያደረገዉን ጥሪ ተከትሎ ነዉ የክልሎች ልዩ ሀይሎች ወደ ግዳጅ […]