loading
ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ።

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ። ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የታጠቁ ወታደሮች ተልዕኮና ማንነታቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ ታዉቋል። ከሁለት ቀናት በፊት ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የተጠረጠረው አንቶኖቭ አውሮፕላንና አሳፍሯቸው የነበሩት 40 የታጠቁ ወታደሮች በመቀሌው የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን […]

በሀዋሳ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ፡፡

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሀዋሳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከ 1 ወር በላይ የቆዩ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደ የቀያቸዉ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ አቶ ሚሊዩን ተፈናቃዮቹ የሚመለሱባቸዉ መንደሮች የቀድሞ ሰላማቸዉን ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስ ቤተሰብ ላላቸው በወር 4 ሺ ብር ፤ቤተሰብ ለሌላቸው ደግሞ በወር 2 ሺ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ድርጊት አወገዘች።

ቤተክርስትያንዋ ሰባት አብያተ ክርስትያናት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የካህናት ህይዎት ማለፉንም ተናግራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል በተፈጸመው ድርጊት ሳቢያ የሰው ህይዎት በመጥፋቱ ማዘናቸዉን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም የሰላማዊ ሰዎች ህይዎት ማለፉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፥ በሁኔታው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል። አሁን ላይ አብረው በኖሩ ወንድማማች ህዝቦች […]