loading
ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012  ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡በሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች የ1ኛ አመት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ተካሂዷል። ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እንዲሁም […]

በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች የሚልከውን ድጋፍ እንዳይደርስ በማገዷ በጋዛ የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ነው የተነገረው፡፡ አሜሪካ ለፍልስጤም ስደተኞች የሚሆን በዓመት 360 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ ማቆሟ ደግሞ ጉዳቱን ያባባሰው ሌላኛው ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የምግብ […]

የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።በመርሀግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተዋል።ጀነራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።የመታሰቢያ መርሀግብሩ እየተከናወነ ያለውም […]

የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::በየኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ልዩ መልዕክተኛ በሰጡት ማረጋገጫ ሀገሪቱ የሚጠበቅባትን መዋጮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መክፈል ባለመቻሏ ነው ማዕቀቡ የተጣለባት፡፡ሺንዋ የዜና ወኪል እንደዘገበው ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት ያልከፈለችው ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመዋጮ እዳ አለባት ፡፡በዚህም መሰረት ግዴታዋን ተወጥታ ህብረቱ ውሳኔውን ካላነሳላት ደቡብ […]

በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር በግብጽ በኩል የተፈፀመዉን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን ኤጀንሲዉ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር በግብጽ በኩል የተፈፀመዉን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን ኤጀንሲዉ አስታወቀ፡፡ጥቃቱ ቢፈጸም ኖሮ ፤ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖሊቲካዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡ኤጀንሲዉ ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14 2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ […]

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012  በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው። በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል። የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው […]

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፕዚዳንት ሎረን ባግቦን የይግባኝ ክርክር መስማት ጀመረ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፕዚዳንት ሎረን ባግቦን የይግባኝ ክርክር መስማት ጀመረ::ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን ኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦ ከቀረበባቸው ክስ ነፃ ናቸው ማለቱን ተከትሎ አቃቤ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው ዳግም ጉዳያቸው መታየት የጀመረው፡፡ የባግቦን የክስ ሂደት የያዙት ጋምቢያዊቷ አቃቤ ህግ ፋቱ ቦም ቤንሶዳ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ህጋዊም ስነስርዓታዊም ስህተቶችን ሰርቷል […]

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ እንደሚያስተሳስር ኬንያውያን ምሁራን ገለፁ።

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ልማት እና ውህድት ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀዉ የዙም የገፅ ለገፅ ውይይት ነዉ ኬኒያዊዉ ሙሁር ሃሳባቸዉን የገለጹትኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ተፈጥሮኣዊ ኃብት የማንንም ፈቃድ እና ችሮታ ሳያስፈልጋቸው የማልማት መብት እንዳላቸው ምሁራኑ እንደሚገነዘቡ ገልፀው በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረሙ ስምምነቶች ተቀባይነት […]

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::ሩሲያ በፈረንጆቹ ጁላይ 1 ላይ ህገ መንግስት ለማሻሻል የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ልታካሂድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ በህዝበ ውሳኔው መሰረት ህገ መንግስቱ ይሻሻል የሚለው ድምፅ የሚያሸንፍ ከሆነ ፑቲን ተጨማሪ ሁለት የምርጫ ውድድሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸው እድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡ በዚህም […]

የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አሁንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ትልቅ ፈተና ነው ሲሉ አስጠነቀቁ::

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አሁንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ትልቅ ፈተና ነው ሲሉ አስጠነቀቁ:: የአሜሪካ የበሽታዎች መቀጣጠርና መከላከል ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሮበርት ሬድፊልድ ወረርሽኙ ሀገሪቱንአንበርክኳታል በማለት ነው የሁኔታውን አስከፊነት የገለፁት፡፡የዋይት ሀውስ የኮቪድ 19 መከላከል ግብረ ሀይል ሀላፊና የተላላፊ እና ኢንፌክሽን ህመሞች ኤክስፐርት የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውችም ይህንኑ ሀሳብ እንደሚጋሩት ተናግረዋል፡፡ ሲ ጂ ቲ […]