loading
የሕወሃት ትንኮሳ በሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭት ላይ የፈጠረው ጫና…

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን ወደሌሎች ክልሎች በማስፋቱ የእርዳታ እህል ለማጓጓዝ መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ:: መንግስት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲል ያሳለፈውን የተናጠል ተኩሱ አቁም አሸባሪው ህወሓት ወደ ጎን በመተው ትንኮሳውን ወደ አማራ እና አፋር ክልል ማስፋቱ ይታወቃል። በዚህ ግጭት ምክንያትም የእርዳታ እህል እና መሰል ድጋፎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት መቸገሩን የተባበሩት […]

በማይካድራ በርካታ የጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል-ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 30 በማይካድራ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ከ1 ሺህ 600 በላይ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በማይካድራው በደረሰው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ላይ ስድስት ወራት የፈጀ ጥናት ሠርቻለሁ ብሏል፡፡ የጥናቱ ዓላማ ድርጊቱን ለዓለም አቀፍ ማኀበረሰብ ማሳወቅ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተጎዱ ወገኖች እንዲካሱ ማድረግ ነው ተብሏል። በጥናቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለዓመታት […]

በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡ ለአንድ ወር ያህል በዘለቀው የደቡብ አፍሪካ ብጥብጥ እስካሁን የ 347 ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 79 የሚሆኑ ሰዎች በጋውንቴንግ ግዛት 276 ዜጎች ደግሞ ክዋዙሉ-ናታል ግዛት መሞታቸውን ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ሁከቱ በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን […]

ለሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ፡፡ በጀርመን ሙኒክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። በተለያዩ ዘርፎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር “ደግሞ ለዓባይ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቦንድ […]

ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013  ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመላው አሜሪካ በርካታ በቀላሉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች አሁንም ክትባት አላገኙም ብለዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የበሽታውን ስርጭት ለማሰፋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፋውቺ፡፡ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ስርጭት የሥርጭት […]

ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም ድጋፍ ጠየቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ጠየቀች፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ብለው የጠሩት የእሳት አደጋ በአስር ሺዎች ሄክታር የሚለካ መሬት መሸፈኑ ተነግሯል፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ሳርዲኒያ በተባለች ደሴት ሲሆን በርካታ የደሴቷ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከአደጋው ለማዳን መኖሪያ አካባቢዎቻቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ፈረንሳይና ግሪክ የጣሊያን መንግስት ያቀረበውን የድጋፍ […]

ሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው ህወሃት ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ መጠቀሙን ቀጥሏል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 21፣ 2013  አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል ፈንተ-ረሱ በከፈተው ጥቃት አሁንም ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ እየተጠቀመ ይገኛል። የሃገር መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ሃይል በግንባሩ እየወሰዱት ባለዉ እርምጃ ጅንታዉን ከአካባቢዉ የማጽዳት ዘመቻ ተጨማሪ ለውጊያ ያልደረሱ ታዳጊዎች ተይዘዋል።  በግንባሩ ህብረሰተቡን በማስተባበር ስራ ላይ የሚገኘዉ የክልሉ ማረሚያ ቤት ምክትል ኮሚሺነር አቶ መሀመድ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት […]

መንግስት 41ሺህ 485 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ መመለሱን ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 21፣ 2013  የኢትዮጵያ መንግስት 80 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 41ሺህ 485 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ እንዲመለሱ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ምላሽ ማእከል ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ወገኖችን በመቀበል እና በማስተናገድ እንዲሁም ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ በማድረግ እየሰራ እንደሆነ የኮሚሽኑ […]

ኢዜማ ያቀረበዉ የይግባኝ አቤቱታ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ኢዜማ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀበለ፡፡ ፍርድቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ እንደሰጠዉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ ) በማህበራዊ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢዜማ በ28 ምርጫ […]

ለህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው የተሰበሰበ ገንዘብ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 ለህዳሴ ግድብ በዚህ ዓመት ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ ከዳያስፖራው ተሰበሰበ:: የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪ ብሔራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ  ላለፉት 10 ዓመታት ዳያስፖራው በቦንድ ግዢ እና በስጦታ ያደረገው ድጋፍ ከ 1 ነጥብ 5 በሊዮን ብር በላይ ነዉ፡፡ የውሃ ሙሌትተከትሎ በተፈጠረው መነሳሳት ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገ  ነው፡፡ከዚህ […]