
በሰሜን ምእራብ ናይጀሪያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 23 ወታደሮች ተገደሉ፡፡
አዲስ አበባ፣ሐምሌ13፣ 2012 በሰሜን ምእራብ ናይጀሪያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 23 ወታደሮች ተገደሉ፡፡ ታጣቂዎቹ በካትሲና ግዛት ጂቢያ በተባለው አካባቢ በአንድ ጫካ በሚዘዋወሩበት ወቅት ወታደሮቹላይ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጉዳቱን ያደረሱት፡፡ አልጀዚራ እንድዘገበው ከሞቱት በተጨማሪ ከጥቃቱ በኋላ የገቡበት ያልታወቀ የሰራዊቱ አባላት መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ከአሁን ቀደም በአካባቢው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከብቶችን ዘርፈው እና ሰዎችን አግተው ሲሰወሩ ከቦኩሃራም ጋር ግንኙነት […]