loading
በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013  በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ:: ድርጅቱ በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው በአውሮፓ በሳምንት ውስጥ የበሽታው ስርጭት በማርች ወር ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር የበለጠ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ አህጉር ሪጂናልን ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሃንስ ክሉግ አሁን ላይ በአህጉሩ እየታየ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለዋል፡፡ በአወሮፓ […]

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ለማስጀመር የሚያስችል ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ለማስጀመር የሚያስችል ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ ::ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ማስጀመር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል። በጉባኤው ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኘተዋል።በጉባኤው ዩኒቨርሲቲዎች የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከል […]

በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡የእንግሊዝ ጤና ሃላፊ ማት ሃንኮክ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጫፍ ላይ መድረሱን የተናገሩ ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ተጨማሪ ክልከላዎች ሊተገበሩ ይገባል ብለዋል፡፡አሁን ላይ ያለን ምርጫ ክልከላዎችን በማያከብሩ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመር አለብን ብለዋል ዋና ፀሐፊው፡፡ በመንግስት በኩል የተቀመጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክልከላዎችን […]

የኮትዲቯር ህዝባዊ አመፅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013  የኮትዲቯር ተቃዋወች በፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ላይ ህዝባዊ አመፅ እንዲቀሰቀስ ጥሪ አስተላለፈፉ::የተቃውሞው መነሻ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2010 ወደ ስልጣን የመጡት ኦታራ በ2015 ዳግም ተመርጠው ሀገሪቱን እያስተዳደሩ የሚገኙ ሲሆን አሁን ለሶስተኛ ጊዜ እወዳደራለሁ ማለታቸውን ህገ መንግስቱ አይፈቅድላቸውም የሚል ነው፡፡ በሀገሪቱ የብዙ ተቃዋሚ ፓርቲወች ስብስብና ዋነኛ የምርጫው ተቀናቃኝ ሆኖ የቀረበው ፓርቲ የኦታራ እንቅስቃሴ […]

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጠ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጠ::ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት ሽብርተኝነትን መከላከልና ማክሸፍ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ያጠነጠነ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል። ስልጠናው ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ ከሪፐብሊካን ጋርድና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ልዩ ኃይል ለተውጣጡ አመራሮችና አባላት ነው የተሰጠው።ሽብርተኝነትን መከላከልና […]

የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ በቨርቹዋል በተካሄደው 75ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢራን በአሜሪካ ምርጫም ሆነ በውስጥ ጉዳይ ላይ በጭራሽ መደራደሪያ ሆና አትቀርብም ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው የሀገራችን ክብርና ብልጽግና ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊያችን ነው ያሉ ሲሆን […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው የ”ገበታ ለሀገር” መርሃ ግብር የሸገር ፕሮጀክት ተከታይ ምዕራፍ ነው። በኢትዮጵያ ጎርጎራ፣ ኮይሻና ወንጪ የሚገነቡት “የገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።በመሆኑን ዓለም […]

በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በሞዛምቢክ እየተባባሰ የመጣው የሽብር ጥቃት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት ዳርጓል ተባለ:: በሀገሪቱ በምንግስት ወታደሮች እና ነፍጥ አንግበው ጥቃት በሚያደርሱ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በርካታ ዜጎችን የእንግልትና የስቃይ ሰለባ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ በተባለው አካባቢ ታጣቂዎቹ የሚያደርሱት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህም […]

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል:: ማሊ ማእቀቡ የተጣለባት ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር በበላይነት የመራው ኢኩዋስ ማእቀቡ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለዓርብ […]

ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች:: በዓሳ ሀብት ልማት ተቋም ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ግለሰብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀችው ሴኡል በመጨረሻ በሰሜን ኮሪያ የባህር ጠረፍ አስከሬናቸው መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሰውየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ገድለው ሲያበቁ በጭካኔ አስከሬናቸው […]