loading
መንግስት የተገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የታለመላቸውን አላማ እያሳኩ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

መንግስት የተገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የታለመላቸውን አላማ እያሳኩ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር ጋር በመሆን ከ2007-2010 ዓ/ም ያከናወነውን የኢንዱሰትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን የኦዲት ውጤትን ለኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎች አቅርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በቋሚ ኮሚቴው የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ተገንብተው ያለቁ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች መንግስት የፈለገውን አላማ እያሳኩ አይደለም ብሏል፡፡ በዚህም የሚጠበቅባቸዉን ያህል የውጭ ምንዛሬ እያመነጩ እንዳልሆነ አስታውቋል።

በቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት፤ ከቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክ 130 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው 16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው።

ከሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ 50 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም የተገኘው 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ጠቅሷል።

በሪፖርቱ በግንባታ ላይ ያሉትም የኢንዱሰትሪ ፓርኮች በተያዘላቸው ጊዜና በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ እየተሰሩ እንዳልሆነ ተገልጿል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ለሊሴ ነሜ በሰጡት ማብራሪያ፤ የአዳማ߹ የድሬዳዋ߹ የጀማ߹ የቂሊንጦና የቦሌ ለሚ ቁጥር 2 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ደረጃ ከታቀደው አንፃር አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበዉ መንግስት መሰረተ ልማት አለመዘርጋቱ߹ የበጀት ዕጥረትና የሰራተኛ ፍልሰት߹ በአገሪቱ ተከስቶ የነበረ አለማረጋጋት እንደ እንቀፋት አንስተዋል።

ወ/ሮ ለሊሴ ኮርፖሬሽኑ ክፍተቱን ለመሙላት ሰፊ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ የመንግስት እና የባለድርሻ አካላት ርብርብ ውስን መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *