በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል
በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል
የካታላኑ ባርሴሎና በስፔን የንጉስ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ራሞን ሳንቼዝ ፒዡዋን አቅንቶ በሲቪያ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዶ ተመልሷል፡፡
በሙሉ ጨዋታው አምበሉ ሊዮኔል ሜሲ ባርሳን ያላገለገለ ሲሆን አዲሱ ፈራሚ ኬቨን ፕሪንስ ቦአቲንግ ለቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን ማድረግ ቢችልም በሁለተኛው አጋማሽ በሊዩስ ሱሬዝ ተቀይሮ እስከጣበት ጊዜ ድረስ ማራኪ እንቅስቃሴ ማሳየት አልቻለም፡፡
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ያልተስተናገደ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ግን ፓብሎ ሳራቢያ እና ዊሳም ቤን ያድር ያስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች የአንዳሉዥያውን ቡድን አሸናፊ አድርገውታል፡፡
የአራት ዓመት የኮፓ ዴል ሬይ የበላይነቱ አደጋ ላይ የወደቀው ባርሳ፤ በመልሱ ግጥሚያ ካምፕ ኑ ላይ በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፍ ግድ ሁኖበታል፡፡
ዛሬ ምሽት ሁለት የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ፍልሚያዎች ሲካሄዱ 5፡30 ሲል ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ቤርናባው ጅሮናን ያስተናግዳል፡፡ ኢስፓኞል ደግሞ ከሪያል ቤቲስ ይጫወታሉ፡፡