loading
በበርሊን ማራቶን ኬንያዊው ኢሉይድ ኪፕቾጌ የአለም ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆን ችሏል

አርትስ ስፖርት 06/01/2011
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የBMW 2018 በርሊን ማራቶን ውድድር ኬንያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሁነዋል፡፡
በወንዶች የተካሄደውን ፉክክር ኬንያዊው የ33 አመት አትሌት ኢሉይድ ኪፕቾጌ 2፡01፡39 በሆነ ጊዜ በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ከአራት አመት በፊት በዴኒስ ኪሜቶ (2፡02፡57) ተይዞ የነበረውን የአለም ክብረወሰን በ1 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማሻሻል አሸናፊ ሁኗል፡፡
ከውድድሩ በኋላ ኪፕቾጌ ‹‹አሁን የሚሰማኝን ስሜት ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል›› ሲል ተናግሯል፡፡
የሀገሩ ልጆች የሆኑት አሞስ ኪፕሩቶ 2፡06፡23 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሲሆን ዊልሰን ኪፕሳንግ 2፡06፡48 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡
በሴቶች የተደረገውን ውድድር ኬንያዊቷ ግላዲስ ቼሮኖ በ2፡18፡11 ቀዳሚ በመሆን ስታጠናቅቅ የባለፈው አመት ክብሯን ማስጠበቅ ችላለች፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ በ23 ሰከንዶች ዘግይታ በመግባት በ2፡18፡34 ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ፤ ውድድሩ ሲጀመር መሪ የነበረችው ጥሩነሽ ዲባባ በ2፡18፡55 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *