በቡራዩ ተከስቶ ከነበረው ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች 322 ተለቀቁ
አርትስ 14/02/2011
ከዚህ ቀደም በቡራዩ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት 630 ወጣቶች ከተከሰተው ችግር ጋር ግንኙነት ያሌላቸው መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ 322 ወጣቶች ስልጠና ወስደው መለቀቃቸው ተገለፀ፡፡
የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽ ቢሮ እንደገለፀው የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ አስተባባሪ ኮማንደር በቃና ሚደቅሳ እንደገለጹት፣ 322 ወጣቶች በቡራዩና በአዳማ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ነው የተለቀቁት፡፡
የተቀሩት 308 ለተፈጸመው ወንጀል ተጠርጣሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ መሆናቸውን ኮማንደር በቃና ገልጸዋል፡፡