loading
በአዲስ አበባ 161 ሺ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት የተያዘው ዕቅድ የሚበረታታ ነው አሉ የአሜሪካው አምባሳደር ማይክ ሬይነር

አርትስ 14/02/2011

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የአሜሪካውን አምባሳደር ማይክ ሬይነርን በፅ/ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋግረዋል።በውይይታቸውም በአካባቢ ጥበቃ እና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ አሜሪካ የቴክኒክ ድጋፍለማድረግ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደሩ ተናግረዋል።በተመሳሳይ የከተማ አስተዳደሩ 161 ሺ ወጣቶች በዚህ አመት ወደ ስራ ለማስገባት የያዘው እቅድ የሚበረታታ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ ለወጣቶቹስልጠና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ሲል የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ በበኩላቸው አዲስ አበባን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግአስተዳደሩ የእንጦጦ ተራራን መነሻ በማድረግ የቱሪዝም ማዕከል ለመገንባት የያዘውን ዕቅድ ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።  ለዚህ ፕሮጀክት ስኬታማነትም በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *