በኤምባሲዎች ስም በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ዕቃ ተያዘ
አርትስ 13/02/2011
ግምቱ 20 ሚሊየን ብር የሚደርሰዉ እቃ የተያዘዉ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነዉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የህግ ማስከበር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ምህረተአብ ገብረመድህን ለፋና እንደተናገሩት፥ በሁለት ኤምባሲዎች እና በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ስም በህገወጥ መንገድለዲፕሎማቲክ አገልግሎት በሚል የገቡ ዕቃዎች ተይዘዋል።
ከአንደኛዉ ኤምባሲ የተያዙት ዕቃዎችም የደህንነት ካሜራዎች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ባለ 65 ኢንች በርካታ ቴሌቪዥኖች ናቸዉ ተብሏል።
የቀረውን ኤምባሲ እና ዓለም አቀፍ ተቋም ዕቃዎች በተመሳሳይ መልኩ እንዲከፈቱ እንደሚደረግ ነው ያስታወቁት።
አቶ ምህረትአብ የኤምባሲዎቹን እና ዓለም አቀፍ ተቋሙን ማንነት ከመግለፅ ተቆጥበዋል።