loading
በእስር የሚገኙት የሳውዲ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተሸለሙ

አርትስ 15/1/2011
ሽልማቱን ያገኙት የሳውዲ መንግስት ከ10 እስከ 15 ዓመት ፈርዶባቸው በእስር ቤት የሚገኙት አብዱላህ አል ሀሚድ፣ ሞሀመድ ፋሀድ አል ቃታኒ እና ዋሊድ አቡ አል ካይር የተባሉት የመብት ተሟጋቾች ናቸው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ተሸላሚዎቹ በሳውዲ አረቢያ ሙስና እንዲጠፋ፣ የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ ህገ ምንግስታዊ አስተዳር እንዲመሰረት ከመንግስት ጋር በሰላማዊ መንገድ ትግል አካሂደዋል፡፡
ሆኖም ይህ እንቅስቃሴያቸውን ያልወደደላቸው የሳውዲ መንግስት ሶስቱንም ግለሰቦች ጥፋተኞች ናችሁ ብሎ ወደ እስር ቤት አስገብቷቸዋል፡፡
የኦልተርኔቲቭ ኖቤል ፕራይዝ አሸናፊዎቹ ለሰው ልጅ ባበረከቱት መልካም ነገር በጋራ የ113 ሺህ 400 ዶላር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የገንዘብ ሽልማቱን ያበረከተላቸው ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ የተባለ ድርጅት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *