አሜሪካ ሳዑዲ አረቢያ ላይ እገዳ ልትጥል እንደምትችል ፍንጭ ሰጠች
አርትስ 14/02/2011
አነጋጋሪ በሆነው የጋዜጠኛ ጀማል ካሹጊ ጉዳይ ሳዑዲ የሰጠችውን ምላሽ አሜሪካ አስነዋሪ ስትል በተደጋጋሚ እያወገዘች ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዎል ሰትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቆይታ በጋዜጠኛው ግድያ ላይ የሳውዲ የቀድሞ ነገስታት እጃችው እንዳለበት እንደሚጠረጥሩ ተናግረው የአሁኑ የሳውዲ ንጉስ ልዑል ሳልማን ስለ ወንጀሉ ብዙም መረጃ ያላቸው አይመስለኝም ብለዋል፡፡
ትራምፕ የትኛውም አካል ቢያቀናብረው ያ አካል ከባድ ችግር ውስጥ እንደገባ ማወቅ አለበት እያሉ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዎ በበኩላቸው አሜሪካ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ለመቅጣት የቪዛ እገዳ ጭምር ልትተገብር እንደምትችል አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ማዕቀብ እስከመጣል የሚደርስ እርምጀ እንወስዳለን በማለት ደጋግመው አስጠንቅቀዋል፡፡