loading
አንካራ እና ሞስኮ በሶሪያ ሰላም ለማስፈን እየመከሩ ነው፡፡

አንካራ እና ሞስኮ በሶሪያ ሰላም ለማስፈን እየመከሩ ነው፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርኩ አቻቸው ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት ያለውን ችግር በጋራ ለመፍታት የሚያስችላቸውን ስምምነት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው በኑርሳ ሚሊሻዎች ቁጥጥር ስር ያለቸውን የኢድሊብ ግዛት ነፃ ለማውጣት ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ቀደም ሲል ተወያይተዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ  ቤት እንዳለው በአካባቢው ያለውን ምስቅልቅል ሁኔታ በፍጥነት ወደነበረበት ለመመለስ  ሞስኮ እና አንካራ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከኤርዶሃን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ በኢድሊብ ያለው ችግር ቀላል እንዳልሆነ እና በመፍትሄዎቹ ዙሪያ በሰፊው መምከራቸውን ገለፀዋል፡፡

ቱርክ እስካሁን በአካባቢው ሰላም እንዲመጣ ጥረት ብታደርግም የእኛም እገዛ ተጨምሮበት የሽብርተኞችን ቡድን በጋራ መዋጋት እንደሚያስፈልግ ተስማምተናል ብለዋል ፑቲን፡፡

ሁለቱ መሪዎች ዳግም በቅርብ ጊዜ ተገናኝተው በሶሪያ ጉዳይ እንደሚመክሩ እና ሩሲያ የውይይቱን ጊዜና ቦታ እንደምታመቻች ተገልጿል፡፡

በሶሪያ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት መፈፍትሄ እንዲያገኝ በተባበሩት መንግስታት ድጋፍ   የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ቢታሰብም ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና እንግሊዝ አለመስማማታቸው ገርሞኛል በማለትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል የሩሲያው ፕሬዝዳንት፡፡

 

ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *