ከ379 ሚሊዮን ብር በላይ የግብርና ታክስ ውዝፍ ባለባቸው 18 ግብር ከፋዮች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ
አርትስ 21/02/2011
ከ379 ሚሊዮን ብር በላይ የግብርና ታክስ ውዝፍ ዕዳ ያለባቸው የ18 ግብር ከፋዮች 10 ቤትና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ ለመንግስት ገቢለማድረግ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
ዉዝፍ ዕዳዉ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ዕዳዉን እንዲከፍሉ ከአንድ አመት በፊት የተነገራቸዉና የማግባባት ስራ ቢሰራም ግብር ከፋዮቹ ይህን ዕድልመጠቀም አለመፍቀዳቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
የባለስልጣኑ የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ንጉሴ ለፋና እንደተናገሩት እስከአሁን ዕዳ ካለባቸው 18 ግብር ከፋዮች ውስጥ11 ግብር ከፋዮች ላይ 135 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር እና ዕዳ ካለባቸው ሁለት ግብር ከፋዮች ቤትና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችን ባለስልጣኑ መዉረሱን ገልጸው ሶስቱ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ ግምት ወጥቶላቸዋል፡፡
ከሌሎች ሰባት እዳ ካለባቸው ግብር ከፋዮች ደግሞ 243 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ዕዳ ያለባቸውን ስምንት ቤቶችን እንዲታገዱ መደረጉ የተገለጸ ሲሆንቤቶችን ለመረከብ ባለስልጣኑ በሂደት ላይ ይገኛል ተብሏል።