loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ አማካኝነት የተደረሰውን የጅቡቲና የኤርትራ ስምምነት አደነቀ

አርትስ 5/13/2010
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ አማካኝነት የተደረሰውን የጅቡቲ እና የኤርትራ ስምምነት አድነቀዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ፀህፈት ቤት በድረገፁ እንዳስነበበው ዋና ጸሃፊው ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን እንዲቻል የደረሱበት የጋራ ስምምነት ለምስራቅ አፍሪካ እና ለሌሎች አገሮች ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
ጉቴሬዝ አያይዘውም አገራቱ አሁን እያስገኙ ያሉት በጎ ጅምሮች እንዲጠናከሩ ለማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከጎናቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር ወደ ኤርትራ በሄዱበት ወቅት በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠሩት ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጅቡቲ በተገኙበት ወቅት ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ ጋር ያለውን ችግር እንድንፈታ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ማመስገናቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *