የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ21ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከሱዳን ጋር ተፈራረመ
ሽንዋ እንደዘገበዉ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት በሰሜን ሱዳን ዋይት ናይል ግዛት መጠለያ ዉስጥ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ለመደገፍ 21 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከሱዳን ጋር ተፈራርሟል፡፡
ትናንት በተደረገዉ ስምምነትም ለስደተኞቹ የሚደረገዉ ድጋፍ 3 ደረጃዎች ያሉት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፉም ለግብርና መገልገያ መሳሪያዎች የሚውል ሲሆን ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተይዞለታል ተብሏል፡፡
ድርጅቱ የሚያደርገዉ ድጋፍ ስደተኛዉ በግብርና ዘርፉ ላይ ተሰማርቶ ዉጤታማ እንዲሆን የሚያግዝና በስፍራዉ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል ነዉ ሲሉ የዋይት ናይል ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነሩ ሃማድ አል ጂዙሊ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነሩ እነደገለጹት በሰሜን ሱዳን ዋይት ናይል ግዛት ከ150 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳን ስደተኞች በመጠለያ ጣቢያ ዉስጥ የሚኖሩ ሲሆን 88ሺህ ያህሉ ደግሞ በተለያዩ ከተማዎች ይኖራሉ፡፡