የአሜሪካ ግዛቶች አስተዳዳሪዎቻቸውን ሊመርጡ ነው ተባለ
አርትስ 15/02/2011
በአሜሪካ 39 ግዛቶች በመጪው ጥቅምት 27 ቀን በሚካሄደው ምርጫ አስተዳዳሪዎቻቸውን እንደሚመርጡ ተነግሯል፡፡
በግዛቶቹ ውስጥ ከሚደረጉት የአስተዳዳሪ ምርጫዎች ውስጥ 35 ያህሉ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነትም የሚካሄዱ ሲሆን ለ435 የእንደራሴ ወንበሮችም ምርጫ ይካሄዳልተብሏል፡፡
እንደአልጀዚራ ዘገባ ይህ ምርጫ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የሚደረገው የአማካይ ዘመን ምርጫ ነው።
የዲሞክራት ፓርቲ ተወካዮች በዚህ ምርጫ ያላቸውን መቀመጫ ከፍ በማድረግ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ፣ በስደተኞች እና ሌሎች ጉዳዮች በሚያሳልፏቸው ውሳኔዎችላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ ተስፋ ጥለዋል፡፡
ሪፐብሊካን ፓርቲ በሴኔቱ 51 መቀመጫዎች ሲኖሩት ዲሞክራት ደግሞ ቀሪዎቹን 49 መቀመጫዎች ይዟል፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ በ100 ሚሊየን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡