የጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር መረጃዎች …
የጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር መረጃዎች …
ጋናዊው የ31 ዓመት አማካይ ኬቨን ፕንስ ቦአቲንግ በውሰት ውል ከሳሱሎ ወደ ባርሴሎና እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ ተቀላቅሏል፡፡
…………………………………………..
የቀድሞ የአርሰናልና ቼልሲ የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ የ38 ዓመቱ እንግሊዛዊ አሽሊ ኮል በሻምፒዮንሽፕ እየተወዳደረ የሚገኘውን ደርቢ ካውንቲ እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ ለልማገልገል ተስማምቷል፡፡
ደርቢ ካውንቲ በፍራንክ ላምፓርድ እየሰለጠነ ሲሆን ላምፓርድ እና ኮል በቼልሲ ቤት በተጫዋችነት አብረው አሳልፈዋል፡፡
…………………………….…………….
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ሀደርስፊልድ ታውን በተሰናባቹ ዴቪድ ዋግነር ምትክ የቦርያ ዶርትሙንዱን የሁለተኛው ቡድን አሰልጣኝ ያን ዚዌርትን ቀጥሯል፡፡
አዲሱ የ36 ዓመት ወጣት አሰልጣኝ ዚዌርት ቡድኑን ከመውረድ እንዲታደጉት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡
…………………………………………..
የማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳያዊያን ተጫዋቾች ፖል ፖግባ እና አንቶኒ ማርሻል የሞሪንሆን ስንብት ተከትሎ ከቀያዮቹ ሰይጣኖቹ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ከክለቡ ሃላፊ ሰዎች ጋር እየተነጋገሩ ነው ተብሏል፡፡
…………………………………………..
አርሰናል የሪያል ማድሪድ እና ኮለምቢያ የጨዋታ አቀጣጣይ ተጫዋች ሃሜስ ሩድርጌዝ በውሰት ውል መነሻ ወደ ለንደን የሚመጣበትን መንገድ እየመረመሩት እንደሆነ ዘ ኢንድፔንደንት አስነብቧል፡፡ ተጫዋቹ በአሁኑ ጊዜ በውስት በባየርን ሙኒክ እየተጫወተ ይገኛል፡፡