ግብፅ በቀይ ባህር የዓሳ ማጥመድ ስራ እንዳይካሄድ ከለከለለች
ግብፅ በቀይ ባህር የዓሳ ማጥመድ ስራ እንዳይካሄድ ከለከለለች
የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው በአካባቢው ስነ ህይዎታዊ ሚዛንን ለመጠበቅ በማሰብ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
የዓሳ ሀብት ልማት ባለስልጣን መስሪያ ቤትን በሀላፊነት የሚመሩት ዶክተር አይመን አማር እንዳሉት በፈረንጆቹ ከየካቲት እስከ መስከረም ለሰባት ወራ ያህል በቀይ ባሀር አካባቢ ዓሳ ማስገር አይቻልም፡፡
የግብፁ አክባር አል ዮም ጋዜጣ እንደዘገበው የሀገሪቱ መንግስት የወሰደው እርምጃ የውሀ ውስጥ ብዛሃ ህይዎት እንዳይጎዳ ያደርጋል፡፡