loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን አወያይተያዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን አወያይተያዋል

ጠቅላይ ሚር ዐቢይ አሕመድ የሀገር ውስጥ ዲፕሎማቶችን በፅህፈት ቤታቸው ሰብስበው    በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዲፕሎማቶቹ ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር ሊመሰርቱ እንደሚገባ በአፅንዖት አሳስበዋል።

በተጨማሪም ዲፕሎማቶቹ የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፤ የሚመደቡባቸውን አገራት ፖሊሲ የመገንዘብ እና በአገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት የማስጠበቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው አስታውሰዋል።

ውይይቱ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የተደረጉትን ለውጦች ለመገምገም በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መሆኑም ታውቋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *