loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍትህና ዲሞክራሲ የሚሸከሙ ተቋማትን በመገንባት ላይ እንገኛለን አሉ

አርትስ 21/02/2011

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ ዛሬ በፍራንክፈርት ለተሰባሰቡ ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ኢትዮጵውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚህ ተስፋ እናደርጋለን ደግሞም እናምናለን በሚል በተጠናቀቀው ንግግራቸው የኛ ለነገው ትውልድ አንፀባራቂ ኢትዮጵያን የመገንባት ግዙፍ ኃላፊነት ተጥሎበታል ብለዋል፡፡ ጊዜው ያላየነውን የምናይበት ያልሞከርነውን የምንሞክርበት ለአገራችን በተባበረ ክንድ የምንተጋበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አብይ ፍትህና ዴሞክራሲ የሚሸከሙ ተቋማትን በመገንባት ላይ እንገኛለን አዲስ የተዋቀረው ካቢኔም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድን ነፃ ፣ተአማኒ እና ገለልተኛ ለማድረግ የህግ ማሻሻያ እየተደረገ ነው ፤የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ጠናካራ ለውጥ በማድረግ ላ እንገኛለን፤ የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያን የሚወክል እና ዘመናዊ እንዲሆን እንዲሆን ከሌሎች አገራት ጋር በመተባበር ጭምር እንሰራለን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ግጭቶችን ማብረድ እና የውጭ ግንኙነትን ማጠናከር ቀን ከሌት የምንሰራበት ጉዳይ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ስደትን በተመለከተም ልጆቻችን ለስደት ወደ አውሮፓ የሚመጡበት ጊዜ ያበቃል በማለት ተስፋቸውን አካፍለዋል፡፡

እንደ ሰሜን አሜሪካው ሁሉ አንድ ዶላር ለህዝባቸው እንዲሰጡም ጠይቀዋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *