ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቫቲካን የሚገኘው የቅዱስ ስቴፋኖስ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቫቲካን የሚገኘው የቅዱስ ስቴፋኖስ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል፡፡
ዶክተር አብይ በሮም ጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንና የቫቲካን ራስ አገዝ ከተማ መሪ ቅዱስነታቸው አቡነ ፍራንሲስን አነጋግረዋል:: በተጨማሪም ከቅዱስ ከተማዋ ዋና አስተዳዳሪ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር በኢትዮጵያና በቫቲካን የጋራ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል::
ጠ/ሚር አብይ በቫቲካን የሚገኘውን የቅዱስ ስጢፋኖስ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያን ጎበኙ:: በጉብኝቱ ወቅትም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በጠ/ሚሩ አነሳሽነት የተገነባውን የሰላም ድልድይ ያስታወሱት ካርዲናል አባ ብርሃነ ኢየሱስ አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በጣሊያኑ ጠ/ሚር ጁሴፔ ኮንቴ አቀባበል በፓላዞ ቺጊ/ብሄራዊ ቤተ መንግስት ተደረገላቸው:: ሁለቱ መሪዎች ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅትም ከአዲስ አበባ ምፅዋ በሚዘረጋው የባቡር ሃዲድ ዙሪያ ትብብራቸውን አንድ ደረጃ ከፍ ስለማድረግ ተወያይተዋል::
በጣሊያን የረጅም ጊዜ የልማት ትብብር መሰረትም ለትምህርት እድሜያቸው የደረሱ ህፃናትን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮግራሞች ላይ ለመስራት ተስማምተዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደዉ የዳፎሱ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እንደሚሳተፉ ታዉቋል፡፡