loading
በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡ በግብፅ ዋና ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ 10 ህጻናትን ጨምሮ 41 ምእመናን ህይወታቸው ማለፉን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በአደጋው ህይወት ለማዳን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ፖሊሶችን ጨምሮ 45 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ጥቂቶቹ ከሆስፒታል መውጣታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


አደጋው በጊዛ ምዕራብ ሙኒራ አውራጃ በሚገኘው በአቡነ ሲፈን ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ የኤሌክትሪክ ችግር መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። እሳቱ የተቀሰቀሰው ቤተክርስቲያኑ በአገልግሎት ላይ ሲሆን የመጀመርያ የፎረንሲክ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት እሳቱ የተነሳው በሁለተኛው ፎቅ የጥናት አዳራሽ ውስጥ ባለው የአየር ማቀዝቀዣ ክፍል በተፈጠረ የኤሌክትሪክ ንክኪ መሆኑን ፖሊስጠቁሟል።


በርካታ ሰዎች ከአደጋው ህይወታቸውን ለማትረፍ ቢጥሩም የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከእሳቱ ነበልባል የወጣው ወፍራም ጭስ ለጉዳቱ እና ሞት ዋና መንስኤ ነው ብሏል። ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ለተጎጂዎች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን የገለፁ ሲሆን ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት አስፈላጊ ድጋፍ እንዲያድረጉና የተጎጂ ሰዎችን የጤና ሁኔታ እንዲከታሉ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *