loading
የኤርትራ ኤምባሲ በአዲስ አበባ እነሆ ተከፈተ

የኤርትራ ኤምባሲ በአዲስ አበባ እነሆ ተከፈተ

ሺዎች ለሞቱበት እና ባለፉት ሃያ ዓመታት ብዙ ቤተሰቦች ለተራራቁበት የኢትዮ ኤርትራ ታሪክ ያለፉት ሳምንታት የተለየ የደስታ ስሜት ፈጥረዋል፡፡ አገራቱ የህዝቡ ስሜት ምን ያህል ተጎድቶ እንደነበር ያስተዋሉበትም ይመስላል፡፡ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ህዝቦች ልብ ውስጥ ከፍተኛ የመገናኘት ፍላጎት ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኤርትራ ጉብኝት ሲያደርጉ ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል የአየር ትራንስፖርት እና የስልክ አገልግሎቱ ተጀምሯል፡፡ ሌላውና ኤምባሲዎቻቸውን መልሶ መክፈት አንዱ እንደመሆኑ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የቀድሞው ኤምባሲ የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ በክብር በመስቀል ፕሬዝዳንቱ በተገኙበት ዛሬ ይኸው ተከፈተ፡፡

የኢትዮጵያውም ኤምባሲ መከፈት ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *