Africa

የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡

የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ማሪታይም አገልግሎት ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትናሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አካላት ያሉበት ግብረ ሀይል የአሰብን ወደብ ስራ ቶሎ ለማስጀመር ተቋቁሟል።

የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በአሁኑ ወቅት የመንገድ ጥገና ስራም እየተካሄደ ይገኛል ያሉት አቶ መለስ በኤርትራ በኩልም ተመሳሳይ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራም በነገው እለት በይፋ እንደሚጀምርም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትኬት ቢሮውን በአስመራ ተከፍቷል ያሉት አቶ መለስ በቀጣይም የበረራ ቁጥሮቹን ከፍ እያደረገ እንደሚሄድ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራ አየር ክልልን በመጠቀሙ በአማካኝ ያጣው የነበረውን 100 ሺህ ዶላር ያስቀርለታል ሲሉም ተናግረወዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነገው እለት በሚጀምረው በረራም 465 ሰዎች ወደ አስመራ እንደሚጓዙም አቶ መለስ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች እና ለዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው የቆዩ ኤርትራውያን ይገኙበታልም ተብሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button