loading
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገር ውስጥና በውጭ የነበሩት ሲኖዶሶች በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ተስማሙ

ባለፉት 27 ዓመት በሁለት ሲኖዶስ ስትመራ የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ወደ አንድ ለማምጣት የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በዋሸንግተን ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ባለፈው
እሁድ የሁለቱም ልኡካን አባቶች በተገኙበት የጋራ ጸሎትና የመክፈቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል።
በእስካሁኑ ውይይታቸው በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተነገረው።
በተጨማሪም “የሀገር ቤት ሲኖዶስ” እና “ስደተኛ ሲኖዶስ” የሚባለውን ለማስቀረት ተስማምተዋል።
ይህ የሰላምና የእርቅ ጉባዔ እስከ አርብ ድረስ የሚቆይ እንደሆነና በውይይቱ መጨረሻ መግላጫ እንደሚሰጥ ነው የተገለፁው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *