loading
በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡

በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡
ፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ ሀገራቸውን ሰላም ከነሳት ነገር የመጀመሪያው የቦኮሀራም ጥቃት ነው ይባላል፡፡
ነገር ግን ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በተደረገ ጥናት ሌላ አስደንጋጭ ክስተት መፈጠሩን የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው በዚህ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከብት አርቢዎችና በአርሶ አደሮች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ1ሽህ 500 በላይ ሰዎች እርስ በርስ ተገዳድለዋል ይላል መረጃው፡፡
ይሄ ደግሞ ቦኮሃራም ባደረሰው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች ቢያንስ በስድስት እጥፍ ይበልጣል ነው የተባለው፡፡
ሰዎቹን ለግጭት የሚያበቃቸው ውሀ፣ እንዲሁም የእርሻና የግጦሽ መሬት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ተመጠጣኝ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር እርምጃ መውሰድ አለበት ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *