loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካን ምክትል ፕሬዝዳንት ያነጋግራሉ::

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ አገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር አብይ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ከሚያራምዱ ኢትዮጵያውያን የፓርቲ መሪዎች ጋር የሚነጋገሩ መሆኑ ታውቋል።
በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ የሀይማኖት አባቶች የእርቀ ሰላም መድረክ ማጠናቀቂያ ላይ በመገኘት ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *