loading
ግብጽ አምስት ሰዎችን በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች፡፡

የግብጽ ፍርድ ቤት የቀድሞውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ መሪ ሞሀመድ ባዲን ጨምሮ አምስት ሰዎች በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል ተብሏል፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው አሁን ከአራት አጋሮቻቸው ጋር የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ባዲ በ2013 ከተያዙ በኋላ በተናጠል ፍርድ ቤት ቀርበው የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን የአቅርቦት ሚኒስትር ባሰም ኡዳን በ15 ዓመት እንዲሁም ሌሎች 3 ሰዎችን በ10 ዓመት እስራት መቅጣቱንም ዘገባው አመላክቷል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *