loading
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡

ተጠርጣሪው የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት ውጭ ሃገር ከሚገኙ በሽብር ድርጊት ውስጥ ከተሰማሩ አካላት ጋር የስልክ ግንኙነት በማድረግ ህገ ወጥ ድርጊቱን አስተባብረዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ነው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙት፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተሰጠው የምርመራ ጊዜ የሚጠበቅበትን ስራ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
ቀሪ የምርመራ ስራውን ለማካሄድም ተጨማሪ 14 ቀን እንዲፈቀድለት ቡድኑ አመልክቷል፡፡
ቀሪ ከተባሉ የምርመራ ስራዎች መካከል የምስክሮችን ቃል መቀበል፣ ውጭ ሃገር የሚገኙ የተጠርጣሪው ግብራበሮች ላይ ብርበራና ሌሎች የምርመራ ስራዎችን ለማካሄድ ከሃገራት ጋር ግንኙነት ማድረግ የሚሉ ተግባራት ይጠቀሳሉ፡፡
ተጠርጣሪው በሃገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶች እጃቸው እንዳለበት የሚያሳይ አዲስ የምርመራ መዝገብ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን የመቀበልና ከገቢያቸው በላይ ሃብት ይዘው ተገኝተዋል በሚል የተጀመረባቸውን ምርመራ ለማጠናቀቅ የሚሉትም ተካተዋል፡፡
ለሽብር ተግባር ከውጭ ሃገር ተላከ ስለተባለው ገንዘብ ያልታወቁ ሰንደቅ ዓላማዎችና እንዲሁም በተያዙ ቦምቦች ዙሪያ ተጨማሪ የማጣራት ተግባርም ተጠቅሷል፡፡
የተጠርጣሪው ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛዬ ላይ መገናኛ ብዙሃን የተዛባ የሚዲያ ሽፋን እየሰጡ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን የሚለውን አቤቱታ በማስቀደም ፖሊስ በድጋሚ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተገቢነት የለውም የሚለውን አንስተዋል፡፡
በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት የተጀመሩ የምርመራ መዛግብት አብዛኞቹ ለክስ እየተዘጋጁ ባሉበት በአሁን ግዜ ይሄኛው የደንበኛዬ ጉዳይ ተለይቶ ሰፊ የምርመራ ጊዜ መፈለጉ ከህግ አንፃር ትክክል አይደለም የሚሉ ምክንያችን በመጥቀስ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲከበር አመልክተዋል፡፡
ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ መገናኛ ብዙሃን የችሎቱን ውሎ በሚገባ በመከታተል የግራ ቀኙን ክርክር በትክክል እንዲዘግቡና የምርመራ ውጤቱን ለመጠባቅ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ 8 ቀን ፈቅዷል::
ኢ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *