loading
ትላንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈጻሚ ሆነዉ የተሾሙት ዶክተር አብርሃም በላይ ማን ናቸዉ?

አርትስ 18/12/2010
ዶክተር አብርሃም በላይ በ1972 ዓ.ም በአዲግራት የተወለዱ ሲሆን ፤ከ1991 ጀምሮ የኢፌድሪ መከላከያ ስራዊት አባል በመሆን እስከ ሌተናል ኮሌኔል ማዕረግ ደርሰዋል፡፡ከ1996-1998 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጂነሪነግ ኮሌጅን በአሰተማሪነት አገልግለዋል፡፡
ከ19 98 ዓ.ም ጀምሮም በተለያዩ ሀላፊነቶች በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግለዋል፡፡
ከ2007-2009 ባለዉ አመት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ የሀገር አቀፍ የምርምር ካዉንስል ቴክኒካል አማካሪ አባል በመሆንም ዶክተር አብርሃም ሰርተዋል፡፡
በ2008ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀዉ የችግር ፈቺ ምርምር ዉጤት ዉድድር ላይ ተወዳድረዉ በማሸነፋቸዉ የ3.9 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የዶክተር አብርሃም የጥናትና ምርምር ዉጤቶቻቸዉ በተለያዩ አለማቀፍ ጆርናሎች የታተሙላቸዉ ሲሆን ሁሉም የጥናታቸዉ ዉጤቶች ትኩረቱ ሀገራዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና ባለቤትነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በተለይ የኤሌክትሪክ ሀይል አመራር ደህንነትና ሞደርናይዜሽን ስርዓቶች ምን መምሰል እንዳለባቸዉ የሚያሳዩ ናቸዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *