loading
ባለፈው ዓመት የ15 ዓመቱን ጥቁር አሜሪካዊ ታዳጊ ተኩሶ የገደለው ፖሊስ ጥፋተኛ ተባለ፡፡

የቀድሞው የቴክሳስ ፖሊስ ኦፊሰር ሮይ ኦሊቨር በመኪና በሚጓዙ ወጣቶች ላይ ደጋግሞ በመተኮስ ነበር ጆርዳን ኤድዋርድስ የተባለውን ታዳጊ የገደለው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ኦሊቨር በሰው መግደልና በጸብ አጫሪነት መንፈስ ጥቃት በማድረስ ወንጀሎች ነበር ክስ የተመሰረተበት፡፡
ይሁንና ጥፋተኛ የተባለው ሰው በመግደል ወንጀል ብቻ ነው፡፡ ኦሊቨር ጥፋተኛ የተባለበት ወንጀል እስከ እድሜ ልክ እስራት ሊያሰቀጣው ይችላል ነው የተባለው፡፡
የጆርዳን ጠበቃ ውሳኔው ለጆርዳንና ለቤተሰቦቹ ወይም ለወጣቶች ብቻ ሳይሆን በነጭ ፖሊሶች ለሚገደሉ ጥቁር አሜሪካውያን የፍትህ ጥያቄን ይመልሳል ብዬ አምናለሁ ብለዋል፡፡
ዋሽንግተን ፖስት በፈረንጆቹ 2017 ብቻ 980 ሰዎች በፖሊሶች መገደላቸውን ሲዘግብ ዘ ጋርዲያን ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር 1 ሺህ 90 ያደርሰዋል፡፡

አርትስ 23/12/2010

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *