EthiopiaPoliticsRegionsSocialUncategorized

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
ሪፖርተር እንደዘገበው የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማንዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ ስለሆነ በተገኘው አጋጣሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሥልጣን በያዙ ማግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደገለጹት፣ የመታወቂያ ጉዳይ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳበት በመሆኑ አሰጣጡን ማስተካከል ይገባል፡፡
በዚህ መሠረት መመርያው የተሻሻለ በመሆኑ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ለውጥ ያመጣል ተብሏል፡፡
የመጀመሪያው በመታወቂያ ላይ ከብሔር ስያሜ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ሲባል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሰጣጡ ዲጂታል ስለሚሆን ሕገወጦችን መለየት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በተለይ ሕገወጥ ጥቅም የሚሹ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ዘዴዎች መታወቂያ በማውጣት ሲያገኙ የቆዩትን ጥቅም እንደሚያስቀር ታምኗል፡፡
ለአብነት በክልል ከተሞች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው በሕገወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ኮንዶሚኒየም ቤት የተቀራመቱትን ዕርምጃ መውሰድ ያስችላል ተብሏል፡፡
የተሻሻለው መመርያ የኮምፒዩተር አመዘጋገብ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ሒደት፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና የመሸኛ ጉዳይን በዝርዝር ይዟልም ተብሏል፡፡

አርትስ 23/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button