loading
ቴሬዛ ሜይ የአፍሪካን ዝምድና በእጂጉ እንፈልገዋለን አሉ፡፡

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር በአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከጀመሩ ዛሬ 3ኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ደቡብ አፍሪካን ቀጥለው ናይጄሪያን የጎበኙት ሜይ ዛሬ ናይሮቢ ገብተዋል፡፡
ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኬንያ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በንግድና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ፡፡
ሜይ ሀገራቸው ከአውሮፓ ህብረት ጋር በፈረንጆቹ በ2019 ሙሉ በሙሉ ከተለያየች በኋላ በአፍሪካ አህጉር በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሰለመሰማራት ማቀዷን ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ በንግድና በኢንቨስትመንት በተነቃቃችበትና በፍጥነት ማደግ በጀመረችበት ወቅት ሀገሬ ያሰበችውን አብሮ የመስራት ትልቅ ዕቅድ ይዤ ወደ አህጉሪቱ በመምጣቴ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሯ፡፡
ቴሬዛ ሜይ ከ30 ዓመት በኋላ ኬንያን የጎበኙ የመጀመሪያዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ ለመጨረሻ ጊዜ በ1988 ኬንያን የጎበኙት ጠቅላይ ሚንስትር ማርጋሬት ታቸር ነበሩ፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *