loading
የ2018/19 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ምሽት 12፡00 በሞናኮ ይፋ ይሆናል፡፡

ለዘንድሮው ተናፋቂ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ሁሉም 32 ተሳታፊ ቡድኖች ተለይተው የታወቁ ሲሆን ቡድኖች ሀገራት በተሰጣቸው ኮፊሸንት እና ባስመዘገቡት የመድረኩ ነጥቦች በአራት ቋት ውስጥ ተካተዋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
ቋት አንድ፡ ሪያል ማድሪድ (የአምናው አሸናፊ)፤ አትሌቲኮ ማድሪድ (ዩሮፓ ሊግ አሸናፊ)፤ ባየር ሙኒክ፤ ባርሴሎና፤ ዩቬንቱስ፤ ፒ.ኤስ.ጂ፤ ማንችስተር ሲቲ እና ሎኮሞቲቭ ሞስኮ፡፡
ቋት ሁለት፡ ቦርሽያ ዶርሙንድ፤ ፖርቶ፤ ማንችስተር ዩናይትድ፤ ሻክታር ዶኔስክ፤ ሮማ፤ ናፖሊ፤ ቶተንሀም እና ቤኔፊካ፡፡
ቋት ሶስት፡ ሊቨርፑል፤ ሻልክ 04፤ ሊዮን፤ ሞናኮ፤ ሲ.ኤስ.ኬ.ኤ ሞስኮ፤ ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨን፤ አያክስ እና ቫሌንሲያ፡፡
ቋት አራት፡ ቪክቶሪያ ፕለዘን፤ ክለብ ብረዥ፤ ጋላታሳራይ፤ ያንግ ቦይስ፤ኢንተርሚላን፤ ሆፈንየም፤ ሬድ ስታር ቤልግሬድ እና ኤ.ኢ.ኬ አቴንስ፡፡
በቋት ምደባው የስድስቱ ታላላቅ ሊጎች አሸናፊዎች በ2017 ኮፊሸንት መሰረት በምድብ አንድ ላይ ሲካተቱ፤ በተጨማሪም የአምናው የሻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ አሸናፊዎችም ተመድበዋል፡፡ ከሁለት እስከ አራት ቋት ያሉት ደግሞ በክለብ ኮፊሸንት ወይም በውድድሩ ተሳትፎ ባገኙት ነጥቦች መሰረት ተደልድለዋል፡፡
በውድድሩ እንግሊዝ፤ ስፔን፤ ጀርመን እና ጣሊያን እያንዳንዳቸው በአራት ክለቦች ሲወከሉ፤ ፈረንሳይ በሶስት፤ ሩሲያ፤ ኔዘርላንድና ፖርቱጋል በሁለት፤፣ ቤልጅየም፣ ሰርቢያ፣ ቱርክ፤ ሲውዘርላንድ፤ ግሪክ፤ ዩክሬን እና ቼክ ሪፐብሊክ በአንዳንድ ቡድኖች ይወከላሉ፡፡
የውድድሩ የፍፃሜ ግጥሚያው በስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ሜዳ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ እ.አ.አ ሰኔ 1/2019 ይካሄዳል ተብሏል፡፡

አርትስ ስፖርት 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *