loading
የአንበሳ ጊቢ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሴ ክፍሎም ከሀላፊነታቸው ተነሱ፡፡

አቶ ሙሴ ከዛሬ ጀምሮ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ በደብዳቤ የገለፁላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ናቸው ብሏል ሸገር ፡፡
የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለከንቲባ ፅህፈት ቤትና ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ቢሮ ባቀረቡት ጥሪ መሰረትም ትናንት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች የአንበሳ ጊቢን ጎብኝተዋል፡፡
በሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 7 አንበሶች በረሃብና በሕክምና እጥረት ሞተዋል፡፡ ያሉትም ቢሆኑ በመልካም ሁኔታ ላይ አይደሉም፡፡
ከንቲባው ከጉብኝታቸው በኋላ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት በቅርቡ በዝንጀሮ የተነከሱትን ግለሰቦች የህክምና ወጪ የከተማ አስተዳደሩ ይሸፍናል ብለዋል፡፡
የአንበሳ ጊቢ ታድሶ በዘመናዊ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል የእድሳት ስራው የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በ9 ወራት ይጠናቀቃል የተባለው እድሳት አሁን ገና 14 በመቶ ላይ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
በእድሳቱ መዘግየትና በጊቢው ውስጥ የሚኖሩ አንበሶችና ሌሎች እንስሳት አያያዝም አሳሳቢ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡

አርትስ 25/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *